የፈዴራል ማረ/ቤት ኮሚሽን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ እና ትጥቅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት አስፈልጓል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የፈዴራል ማረ/ቤት ኮሚሽን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ እና ትጥቅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት አስፈልጓል፡፡
|
ተ/ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
|
1 |
ሬንጀር ኮትና ሱሪ ከነ-መለዮ፣ ሬንጀር ሸሚዝና ሱሪ ከነ-መለዮ፣ መደበኛ ደንብ ልብስ ከነ-መለዮ፣ የመደበኛ ደንብ ልብስ ሽሚዝና ቀሚስ ከነ-መለዮ፣ ሬንጀር ኮትና ቀሚስ ከነ-መለዮ፣ የሱፍ ካፖርት፣ የመደበኛ ደንብ ልብስ ቲ-ሸርት፣ የሬንጀር ቲ-ሸርት፣ ፍሎቨር ሹራብ፣ ብርድ ልብስ፣ ስልፒንግ ባግ፣ ጥቁር ሰማያዊ ፊልድ ጃኬት፣ ሬንጀር ፈልድ ጃኬት፣ የተሟላ የወንድ ግራንድ ዩኒፎርም፤ የተሟላ የሴት ግራንድ ዩኒፎርም፣ የዝናብ ልብስ የጥበቃ፣ የዝናብ ልብስ የቢሮ፣ ጥቁር ቀበቶ፣ የመኮንኖች ኮርደን፣ የፖሊስ ፊሽካ፣ ባለ ሶስት ቀዳዳ ጎሚኒ ቀበቶ፣ የሥራ ቱታ፣ የሥራ ጋወን፣ የሥነ-ሥርዓት ተቆጣጣሪ ጉንጉን፣ የሥነ-ሥርዓት ተቆጣጣሪ የትከሻ ምልክት፣ የሥነ-ሥርዓት ተቆጣጣሪ ሄልሜት፣ የእጅ ካቴና፣ የእግር ሹራብ /ካልሲ/ ረዥም፣ የእግር ሹራብ /ካልሲ/ አጭር፣ አጎበር/ዛንዚራ፣ የወንድ ቦት ጫማ ከነዚፑ፣ የመኮንኖች ቦት ጫማ፣ የሴት ቡትስ ጫማ፣ የወንድ ጉርድ ጫማ፣ የሴት ጉርድ ጫማ ግዥ |
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ።
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለጸ መሆን አለበት፡፡
- የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በፌዴራል ማረ/ቤት ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 150 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ እንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን በትክክል መጻፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኪሚሽን ከፍ ብሎ በሚገኘው ፌዴራል ማረ/ቤት ኮሚሽን ዋናው መ/ቤት 1ኛ ፎቅ የፋይናንስ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ22/3/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ መስብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-1-26-56-65 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፌዴራል ማረ/ቤት ኮሚሽን
