Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከእሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከእሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 - አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ

ሎት 2 - የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

ሎት 3 - የሕትመት ውጤቶች ግዥ

ሎት 4 - የሰራተኛ መታወቂያ፣ የደረት ባጅ ከነማጠልጠያው እና የጠረጴዛ ባጅ

ሎት 5 - የሥራና ደንብ ልብስ እና ተዛማች እቃዎች ግዥ

ሎት 6 - ልዩ ልዩ የአይን መነጽር ግዥ

ሎት 7 – የአይቲ /የመረጃ ቴከኖሎጂ/ እቃዎች

ሎት 8 - የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃዎች ግዥ

ሎት 9 - የሕፃናት አልጋ ወንበር ጠረጴዛ እና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎች

ሎት 10 - የምንጣፍ ሥራ እና የመጋረጃ ሥራ ከነተዛማጅ እቃዎች ጋርና ከነእጅ ዋጋው

ሎት 11 - የጀነሬተር እና ለኢንስታሌሽኑ የሚያስፈልጉ እቃዎች ጨምሮ ከነእጅ ዋጋው

ሎት 12 - የሕንፃ መሳሪያዎች እና የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ

ሎት 13- የፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና እና ስርቪስ ማድረግ እና ለጥገና የሚያስፈልጉ የመለዋወጫ እቃዎች ግዥ

ሎት 14 - የታሸገ ውሃ ግዥ

ሎት 15 - የገብስ ቆሎ የኦቾሎኒ እና ሽንብራ ድብልቅ

ሎት 16 - የሰራተኞች መቀመጫ ተሸከርካሪ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎችና ሌሎች ተዛማጅ እቃዎች ጥገና

ሎት 17 - የካውንተር ሥራ

1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ አንዲሁም 2018 . በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብርሰብሳቢ /ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በጨረታ ሰነዱ ላይ በየሎቶቹ ለጨረታ ማስከበሪያ የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በመመልከት በምትወዳደሩበት ሎት የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ ቢቀርብ ይመረጣል፣

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፣

6. ሎት 11 ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሁለት በተለያየ ኤንቨሎፕ ሲሆን በአንደኛው ኤንቨሎፕ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒው እና ቴከኒካል መግለጫው ኦርጅናልና ኮፒው እንዲቀርብና በቀሪው 13 ሎቶች በዝርዝር ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒውን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 502 ማስገባት አለባቸው፣

7. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያው በወጣ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5 ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል፣

8. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣

9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን 5 ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 መውሰድ ይችላሉ

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች //ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣

11. ቅርንጫፍ //ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻ፡-

መገናኛ 22 ታከሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ሕንፃ 5 ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 ነው::

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የስልክ ቁጥር፡- 011 668 42 07 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ::

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የካ /ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት

3

Save Tender