የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የአምቦ ሪጅን ፅ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለሃያ ሶስት (23) አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለአምቦ፣ ባኮ፣ ቢሎቦሼ፣ ዋዩ፣ ሰዮ፣ ኢጃጂ፣ ጉደር፣ ሸነን፣ ድሬኢንጪኒ፣ ሆርማት፣ ጊንጪ፣ ጀልዱ፣ ካቺሲ፣ አቡና፣ አዲስ አለም፣ ባንቱ፣ ቡሳ፣ አመያ፣ ወሊሶ፣ ስልክአምባ፣ ቱሉቦሎ፣ሰደንሶዶ ጌዶ እና አምቦ ሪጅን ጨምሮ ለሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሚውል የተለያዩ 4 (አራት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/004/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የአምቦ ሪጅን ፅ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለሃያ ሶስት (23) አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለአምቦ፣ ባኮ፣ ቢሎቦሼ፣ ዋዩ፣ ሰዮ፣ ኢጃጂ፣ ጉደር፣ ሸነን፣ ድሬኢንጪኒ፣ ሆርማት፣ ጊንጪ፣ ጀልዱ፣ ካቺሲ፣ አቡና፣ አዲስ አለም፣ ባንቱ፣ ቡሳ፣ አመያ፣ ወሊሶ፣ ስልክአምባ፣ ቱሉቦሎ፣ሰደንሶዶ ጌዶ እና አምቦ ሪጅን ጨምሮ ለሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሚውል የተለያዩ 4 (አራት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
ሎት-1 |
የተለያዩ 4 (አራት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ማለትም ኮትና ሱሪ ባለ ገበር ለደንበኞች አገልግሎት፤ ጃኬትና ሱሪ፤ ቱታ እና ጋዎን የስፌት አገልግሎት ግዥ |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር (1000254843017 EEU Amb District Connection Fee) በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- አምቦ ከተማ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር- የድሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ “ኦሪጅናል እና ኮፒ” በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/004/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-112-609777 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
