Tender Detail

Tender Details

  • Company Abay Bank S.C (ዓባይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ባምቢስ አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-17-60
  • Websitehttps://abaybank.com.et/am/
  • Deadline18 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price250.00
  • opening date2025-11-18 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለዋና መስሪያ ቤት፣ ለዲስትሪክቶች፤ በመላ ሀገሪቱ ለከፈታቸው ቅርንጫፎች እና ወደፊት ለሚከፍታቸው ተጨማሪ ቅርንጫፎች ቢሮዎች የጽዳት አገልግሎት ሰጪ የሆኑ ብቁ ድርጅቶችን (ኤጀንሲዎችን) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


 

የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ዓባ/ፕፕማ/05/11/2025-26

 

ዓባይ ባንክ .. ለዋና መስሪያ ቤት፣ ለዲስትሪክቶች፤ በመላ ሀገሪቱ ለከፈታቸው ቅርንጫፎች እና ወደፊት ለሚከፍታቸው ተጨማሪ ቅርንጫፎች ቢሮዎች የጽዳት አገልግሎት ሰጪ የሆኑ ብቁ ድርጅቶችን (ኤጀንሲዎችን) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ራት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል

  1. ተጫራቾች በሙያው ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ የመንግስት ግብር የተከፈለበትን የታክስ ክሊራንስ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ፣ ... ሰርተፍኬት፣ ቲን ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  2. ተጫራቾች ከፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ከክልልና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች የቅጥር (Employment) ሥራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) ከማንኛውም ባንክ በተሰራ .. ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቢያንስ 120 ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  4. ተጫራቾች የጽዳት አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስገቡት የአገልግሎት ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ (Price Validity Date) መግለፅ አለባቸው ይህም ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀን ማነስ የለበትም
  5. ተጫራቾች የማይመለስ የአገልግሎት ክፍያን 15 በመቶ ጨምሮ ብር 250.00 (ሁለት መቶ አምሳ ብር) በዓባይ ባንክ ቅርንጫፎች በመክፈል እና የክፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ባምቢስ አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8 ፎቅ ዓባይ ባንክ ዋና /ቤት ግዥና ንብረት ማኔጅመንት ዲፓርትመንት በመቅረብ ከጥቅምት 23 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 200 እስከ 1100 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 200 እስከ 600 ዓት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን
  6. ተጫራቾች የጨረታ ነዳቸውን በሠም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው እስከሚዘጋበት እስከ ህዳር 9 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው
  7. ጨረታው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 9 ቀን 2018 . ከቀኑ 830 ዓባይ ባንክ . ዋና መስሪያ ቤት ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8 ፎቅ ግዥ እና ንብረት ማኔጅመንት ዲፓርትመንት የሚከፈት ይሆናል
  8. ከላይ የተጠቀሱ ቅድመ ሁኔታዎችን ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጭ እንዲሆን ይደረጋል
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-557-12-51/011-557-07-53 የባንኩን ግዥና ንብረት ማኔጅመንት ዲፓርትመንት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

 

ዓባይ ባንክ .

ዓባይ-የታላቅነት ምንጭ!

 

Save Tender