ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሰራተኞች የሥራ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ
የሰራተኞች የሥራ ጫማ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/13/2025
- ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሰራተኞች የሥራ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -10፡00 ድረስ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-5፡00 “ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አጠገብ ቴለ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በስም የታሸገ መሆን አለበት።
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሰራተኞች የሥራ ጫማ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን እስከ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ድረስ ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0968135675 ወይም 0968271291 መጠቀም ይችላሉ።
- ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ
