Tender Detail

Tender Details


የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ለመግዛት በተለያዩ ሎቶች በመከፋፈል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ 2018 . በጀት አመት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ለመግዛት በተለያዩ ሎቶች በመከፋፈል በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በልዩ ፍላጎት እቃዎች በኦፊስ ፈርኒቸር፤ በኤሌክትሮኒክስ፣ በህትመት፣ በማጓጓዥያ፣ በንፅህና መጠበቂያ እቃዎች እና የትምህርት ግብአት ላይ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሰብ እና ዋጋ በሠም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሰነዶችን በመለየት 2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርበቻዋል፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (..) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 11ኛዉ ቀን 300 ሠዓት ይከፈታል።
  8. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-0125/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender