ድርጅታችን ሜልባ ፕሪንቲንግ፤ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከ ገላን ሰላሳ የምባል ከባቢ በድርጅቱ ፋብርካ ቅጥር ገቢ ውስጥ ተከማችተው የሚገኘው የህትመት ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሜልባ ፕሪንቲንግ፤ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከ ገላን ሰላሳ የምባል ከባቢ በድርጅቱ ፋብርካ ቅጥር ገቢ ውስጥ ተከማችተው የሚገኘው የህትመት ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- የህትመት ተረፈ ምርት (Signature Paper) መለኪያ በኪሎግራም
- ሽፍሻፈ ወረቀት (Scrap paper) መለኪያ በኪሎግራም
- ኮር ባላ 84cm መለኪያ በቁጥር
- ያገለገሉ እና ቁርጥራጭ ፕልቶች መለኪያ በኪሎግራም
በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ ፍለጎት ያላችሁ ታጫራቾች ከዚህ በታች ባለው መስፈርት መሠረት ጨረታውን መሳተፍ ሚትችሉ መሆኑን እያሳወቀን፣
- ተጫራቾች ህጋዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነዶች (የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምስክር ወረቀትና የቲን ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ማንነታቻውን የሚገልፅ መታወቅያ ይዞ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሸገር ከተማ ገላን ሰላሳ (30) ካለው ፋብርካ ንብረት አስተዳደር ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በሜልባ ፕሪንቲንግ፤ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ በሲፒኦ (CPO) ብቻ አሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጠትን ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- በህትመት ተረፈ ምርት (signature paper) እና ሽፍሳፊ ወረቀት (Scrap paper) ያሸነፈ ተጫረች ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት የሚቆይ የሻጭና ግዥ ውል ከድርጅቱ ጋር ስለምዋዋል፤ የውል ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ (CPO) ብቻ አሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ አስር (10) የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ ገላን ሰላሳ ፋብርካ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ንብረት ዋጋ ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ ዕለት 5፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመክፈት አያስተጋጉልም፡፡
- ሜልባ ፕርንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0924082216/0923003245 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሜልባ ፕሪንቲንግ፤ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ
