የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ ሎት 1. የጽዳት ዕቃዎችን እና ሎት 2. ስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ
ሎት 1. የጽዳት ዕቃዎችን እና
ሎት 2. ስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎች የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምሬንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል
ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝርውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክበተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ከፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመከፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ ነው ::
7. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299263 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ::
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
