Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline26 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-26 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሠራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (ብትን ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ የወንድና ሴት ጫማዎች፣ ቱታ፣ እና ሌሎችም) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሠራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (ብትን ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ የወንድና ሴት ጫማዎች፣ ቱታ፣ እና ሌሎችም) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ዚህ ተጫራቾች፡-

1.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስ ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

2.     የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም ፡፡

3.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልገሎት ዋና /ቤቱ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጫራቾች ዋጋ በግልጽ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 12ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 400 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 430 ይከፈታል፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees & Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ የባንከ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ናሙና የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት ይዞ በመምጣት የጨረታዉ ፈቻ ቀንና ሰዓት ከማለፉ በፊት ለግዥ ቡድን ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

7.     የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስከበሪያ /Performance bond/ የጨረታውን አጠቃላይ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም የባን ጋራንቲ በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees & Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     የጨረታው አሸናፊ ጥሪ በደረሰው 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና /ቤት ቀርቦ የሥራ ውል መፈረም አለበት፡፡

9.     አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአስር ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና /ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራች የሚያቀርበው ዕቃ በሰጠው ናሙና እና መስሪያ ቤቱ በሚመርጠው ቀለም /Color/ እና ልኬት /Size/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡

11. አሸናፊ ሆነዉ የተመረጡ ድርጅቶች የሚያቀርቡት የደንብ ልብስ ዓይነት ቢጠብ ወይም ቢሰፋ ለመቀየር የሚስማሙ መሆን አለባቸ፡፡

12. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

የስደተኞችና ተመሾች አገልግሎት

የእንቁሳል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ

ከፌደራል ፖሊስ ክበብ ፊት

ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31

 

የስደተኞችና ተመሾች አገልግሎት

Save Tender