ድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጂናልና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን፣ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ያላቸውን ልምድ እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ. (C.P.O ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
በጨረታ መክፈቻ ሰዓት የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉለውም ፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ-ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት)፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ ፡- በስልክ ቁጥር 011-157-24-97 / በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
