Tender Detail

Tender Details

  • Company National Election Board of Ethiopia (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)
  • Address ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 115153468
  • Websitehttps://nebe.org.et/
  • Deadline01 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-01 00:00:00
  • Categories Packaging And Labelling , Services

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ የማሸግ አገልግሎት እና የእሸጋ ጥራት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።


 

የምርጫ ቁሳቁስ የእሸጋና የእሽጋ ጥራት ማረጋገጥ

ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: NEBE/NCB/02/2018

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ የማሸግ አገልግሎት እና የእሸጋ ጥራት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት ንድ፡- የአይሲቲ ቁሳቁስ 20 የታብሌቶች 5 1 የማሸግ አገልግሎት እና 55 የሰነድ እና ቁሳቁስ ሳጥኖች የማሸግ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት ሁለት፡- 20 ታብሌቶች 5 1 መታሸጋቸው እና 55 የሰነድና ቁሳቁስ ሳጥኖች የእሸጋ ጥራት ሂደት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ

በዚሁ መሰረት፡-

  1. ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው ፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ምዝገባ ምስ ወረቀት፣ የግብር ሊራንስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው 45 ቀናት ነው።
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
  7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት ለሎት አንድ ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ) ለሎት ሁለት ብር 30,000.00 (ብር ሰላሳ ) በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 22 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  9. ጨረታው ህዳር 22 ቀን 2018 ከሰዓት 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  10. በጨረታው ፈቻ ዕለት የተጫራ አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
  11. ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው / ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

 

ድራሻችን፡- ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- +251 115153468

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

 

Save Tender