የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች የተለያየ መጠን ያላቸውን የጎማ እና ባትሪ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጎማ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሚገለገልባቸው ተሽከርካሪዎች የተለያየ መጠን ያላቸውን የጎማ እና ባትሪ ዓይነቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፦
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ ፣ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ሰዓት አይደሉም።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በማዘጋጀት በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የተጫራቾች ዋጋ በግልፅ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ የሚቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ስራ አፈፃጸም ማስከበሪያ /Performance Bond/ እቃዎቹን ለማቅረብ ያሸነፈበትን አጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል በተረጋገጠ የባንከ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ጥሪው በደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ የስራ ውል መፈረም አለበት።
- አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአስር ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
