Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በተፈቀደ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ በተለያዩ ሎቶች የተዘረዘሩትን ማለትም የፅህፈት ፤የፅዳት፤ የኤሌክትሮኒከስ፣ ፈርኒቸር ፤የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፤ የብስክሌት ጎማና ካላማዳሪ ፤የህንፃና የኮንስትራክሽን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ቁጥር BOA 01/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በተፈቀደ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ በተለያዩ ሎቶች የተዘረዘሩትን ማለትም የፅህፈት ፤የፅዳት፤ የኤሌክትሮኒከስ፣ ፈርኒቸር ፤የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፤ የብስክሌት ጎማና ካላማዳሪ ፤የህንፃና የኮንስትራክሽን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ማቅረብ የሚችል

4. አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴከኒካል ፕሮፖዛል ከኦርጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6, ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200 ብር በመከፈል ቢሮ ቁጥር 14/ገንዘብ ያዥ ከፍል/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውም ግብር ጨምሮ ሎትı ለጽህፈት እቃ 20,000 ብር/ሀያ ሺህ /፤ሎት2 የተለያዩ ቀለሞችና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች 15,000 ብር/አስራ አምስት ሺህ/፤ ሎት3 የፅዳት እቃዎች 20,000 ብር/ሀያ ሺህ/፤ሎት4 የፈርኒቸር እቃዎች 10,000 ብር/ አስር ሺህ/፤ ሎት5 የኤሌክትሮኒከስ 25,000 ብር/ሃያ አምስት ሺህ/፤ ሎት 6 የህንፃ እቃዎች 1000 ብር /አንድ ሺህ ብር/ ፣ሎት7 የብስክሌት ጎማና ካላማዳሪ 600 ብር/ስድስት መቶ/ እና ሎት8 የኮንስትራክሽን እቃዎች 1000ብር /አንድ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /ስፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ ዋና እና ኮፒ በማለት ቴከኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግ ሁለቱንም በሌላ ትልቅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴከኒካል ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ግብርና ቢሮ፤ ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል/ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡

11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ⁄ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058-226- 64-31 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582262891 በመላከ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ

Save Tender