በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የቀረቡ የፋብሪካ ማሽነሪዎችና የቢሮ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ የቀረቡ የፋብሪካ ማሽነሪዎችና የቢሮ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 26/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው የኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ (ዱከም) የሚገኙ የሶስት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ማሽነሪዎች ማለትም (used warping machine fused high temperature & high pressure intelligent dye machine used knitting machine Used electric steam boiler Used industrial washing machine Used Centrifugal hydro-extractor Used pneumatic Steaming Machine used printing & dyeing production line machine used embossing machine እና ሌሎችም) እንዲሁም የዳይፐር ማምረቻ ፋብሪካ ማሽነሪ ማለትም (used Baby diaper production making line machine) በተጨማሪም የፋብሪካዎቹ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
በመሆኑም:
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቮሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት /ስኬጁል/ መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃ ግልፅ |
እስከ 24/03/2018 |
25/03/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡ አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት (ናይል ኢንሹራንስ ህንጻ) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ ከፋብሪካው የማንሳት ፣ የመጫንና የማጓጓዝ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ - 011-470-85-03
ማሳሰቢያ፡- ዕቃዎቹን ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን (ዱከም) በአካል በመሄድ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የጨረታ ሰነድ መሸጫ አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖከ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
