Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተወሰነ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ለምድር ሚዘን አገልግሎት የሚውሉ የAnalogue Indicator, Software, Printer, Computer, Analogue, load cell, Junction box እና መሳሪያዎችን በማቅረብ እና ነባር ሚዛኑ ላይ በመግጠም አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

3 ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግልፅ ጨረታ ሰነድ ቁጥር NCB/OACFLTD/AMF/09/2018

 

በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተወሰነ ሰላ ብቅል ፋብሪካ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ለምድር ሚዘን አገልግሎት የሚውሉ የAnalogue Indicator, Software, Printer, Computer, Analogue, load cell, Junction box እና መሳሪያዎችን በማቅረብ እና ነባር ሚዛኑ ላይ በመግጠም አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በፋብሪካችን እካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በአሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ/
  • ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1000 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል /ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ- ቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  1. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛላቸውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና /ቤት በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተወሰነ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ከማቅረባቸው በፊት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የምድር ሚዛኑን ሁኔታ ማየት ይኖርባችዋል።
  3. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም Bank guarantee ከቴኒካል ፕሮፖዛል ጋር በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 ቀናት ፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን 12ኛው ቀን ከጠዋቱ 500 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 530 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና /ቤት የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተወሰነ 7 (ሰባተኛ) ፎቆ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሑድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  5. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09-65-65-04-81/09-65-65-02-85 በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን /የተወሰነ የአሰ ብቅል ፋብሪካ

 

Save Tender