የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር፡- አ/ድ/መ/-003/2018 /2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆኑ ስቴሽነሪና የህትመት ስራዎች ፤ ካሜራና እክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር፡- አ/ድ/መ/-003/2018 /2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የሆኑ ስቴሽነሪና የህትመት ስራዎች ፤ ካሜራና እክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን የእቃዎቹ ዝርዝር ከታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።
|
ምድብ ቁጥር |
የሚገዙ እቃዎች አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
የስቴሽነሪ እና የህትመት እቃዎች ግዥ |
5000 ብር |
|
ሎት 2 |
ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች |
10,000 ብር |
|
ሎት 3 |
የሳኒቴሽን እና የግንባታ እቃዎች |
5,000 ብር |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600/ ስድስት መቶ ብር/ በአድዋ ድል መታሰቢያ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000613546867 በመክፈል ደረሰኝ ስሊፕ/ ይዞ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል።
- የጨረታው ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ነው።
- ጨረታው በቀን 01/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ማለትም በቀን 01/04/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሎት-1 ይከፈታል። ሎት-2 በ02/04/2018 3፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሎት 3 በ03/04/18 በ3:00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱ ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት የአድዋ ድል መታሰቢያ እስተዳደር ቢሮ ሊቭል -2 ፋይናንስ ክፍል ይገኛል።
አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት አድዋ ድል መታሰቢያ አስተዳደር ቢሮ ፋይናንስ ክፍል
ስልክ ቁጥር:- +251-0990451200
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ
