በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች የተጠቀሱ የእቃ ግዥ ለ2018 በጀት ዓመት አወዳድሮ ግዥዎች መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች የተጠቀሱ የእቃ ግዥ ለ2018 በጀት ዓመት አወዳድሮ ግዥዎች መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ
- ሎት 2. የፕሮቶኮል ልብስ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት አላቂ የጽሕፈት መሣሪያ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) የፕሮቶኮል ልብስ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ደንብ ልብስ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የሥራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው።
- የተሻሎ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- መሉ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ሕጋዊ ማህተም እና ፊርማ ተደርጐበት መመለስ አለበት፤ ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለእያንዳንዱ እቃ ሳምፕል መቅረብ አለበት፡፡
አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ስልክ ቁጥር- 0118-34-09-79
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
