የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/02/2018
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የሚገዛው ዕቃ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የመኪና ጎማ ግዥ |
60,000 |
|
2 |
ሞተር ሳይክል ጥገና አገ/ት ግዥ |
40,000 |
|
3 |
ፈርኒቸር |
60,000 |
|
4 |
ደን ዘር |
20,000 |
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም (e-GP) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ/ ለእያንዳንዱ ሰነድ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የእንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መክተት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ 1 ኦርጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465512116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
