በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት ለህትመት ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ግብዓት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የተለያዩ የህትመት ግብዓት ግዥ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር EMPDE NCB/12/2018
ድርጅታችን ለህትመት ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ግብዓት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን።
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችለሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ Tel /0116 -46–34-81 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
