የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ2018 እና 2019 ዓ.ም በጀት አመት በመአቀፍ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ማዕ2018-2019/ዕግ/ብ.ግ.ጨ/32/3/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የደንብ ልብስ ግዥ
ፌ.ቤ.ኮ /ማዕ 2018-2019/ዕግ/ብ.ግ.ጨ/32/3/2018
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ2018 እና 2019 ዓ.ም በጀት አመት በመአቀፍ የደንብ ልብስ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ማዕ2018-2019/ዕግ/ብ.ግ.ጨ/32/3/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ለኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ የደንብ ልብሶችን ግዥ ተጫራቾችን የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውን እና ዋጋቸውን በተለያየ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ስነ ስርአት ይህንኑ አስመልክቶ ለፌዴራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ሲሆን ከሚፈለገው ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሃ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 15ኛው እስከ ታህሣሥ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሣሥ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ቅጥር ግቢ ያስረክባል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-18-55-36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
