በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የሚሆኑ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ እ/አ/ስ/ስ/አ/ኮ/ቁ.002/2018
የግልፅ ጨረታ ግዢ ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የሚሆኑ የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥዎች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የግዥው ዝርዝር |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን |
|
1 |
1 |
የጽህፈት መሳሪያዎች |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
ዕቃ |
20,000 |
|
2 |
2 |
የፓራሚሊተሪ ሰራተኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ደንብ ልብስ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
50,000 |
|
3 |
3 |
የአደጋ ጠላቂ ዋናተኞች እቃዎች እና ብሪዚንግ አፓራተስ፤ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
100,000 |
|
4 |
4 |
ልዩ ልዩ የእጅ መሳሪያዎች፤ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
20,000 |
|
5 |
5 |
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጀነሬተር እና የአዳራሽ ሳውንድ ሲስተም ከነሙሉ እቃው ተገጥሞ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
60,000 |
|
6 |
6 |
የህጻናት ማቆያ እቃዎች፣ የተለያዩ መጋረጃዎች እና የፕላስቲክ ወንበሮች |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
ዕቃ |
20,000 |
|
7 |
7 |
የተሸከርካሪ መለዋወጫ እና ጎማዎች |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
50,000 |
|
8 |
8 |
የህክምና እቃዎች ግዥ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
40,000 |
|
9 |
9 |
የህትመት ውጤቶች |
ለሁለተኛ ጊዜ |
አገልግሎት |
30,000 |
|
10 |
10 |
ምግብ ነክ የሆኑና ምግብ ነክ ያልሆኑ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
40,000 |
|
11 |
11 |
የጽዳት እቃዎች /የዱቄት ሳሙና/ |
ለሁለተኛ ጊዜ |
ዕቃ |
20,000 |
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፤ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- አግባብነት ያለው ህጋዊ በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ዋና ንግድ ምዝገባ ፍቃድ እና ያቅራቢዎች ምዝገባ በዌብ ሳይት መመዝገቡን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎችና ጉምሩክ ኮሚሽኑ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሁሉም ሎት በተቀመጠው ሲፒዮ (CPO) ገንዘብ መጠን መሰረት ኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ውስጥ ወይም ለብቻው ፖስታ በማድረግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን /ADDIS ABABA CITY ADMINISTRATION FIRE & DISASTER RISK MANAGEMENT COMMISSION በሚል ስም በማሰራት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ መግለጫ ዋናና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒክ መግለጫ ዋናና ኮፒ በማድረግ በአጠቃላይ 2 /ሁለት/ ኦርጅናል እና 2/ሁለት/ ኮፒዎች፤ ቴክኒካል ፕሮፖዛልና ፋይናሻሉን ለየብቻ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኮሚሸኑ መንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ሥራ ክፍል ማስገባት አለባቸው።
- ከ100,000.00 /መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከተጫረቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 59 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ቴክኒካልና ፋይናሻሉን ሰነድ ብቻ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት በተሰጠው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የሥራ ቀን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል ሆኖም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- 011 878 76 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ቅ/ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኝ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 1ኛ ፎቅ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 59 ማግኘት ይቻላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
