የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተለያዩ ፕሮግራሞችና ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች ማለትም የሜካኒክስ ፣ የእውቶሞቲቭ ፣የአይሲቲ ፣ የቢኢአይ ፣ የኮንስትራከሽን፣ የሰርቬ ፣የስቴሽነሪ ፣ የደንብ ልብሶች፣ የፅዳት፣ የመኪና መለዋወጫ ፣ ለሆቴል እና ቱሪዝም ስልጠና መስጫ እቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተለያዩ ፕሮግራሞችና ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎች ማለትም የሜካኒክስ ፣ የእውቶሞቲቭ ፣የአይሲቲ ፣ የቢኢአይ ፣ የኮንስትራከሽን፣ የሰርቬ ፣የስቴሽነሪ ፣ የደንብ ልብሶች፣ የፅዳት፣ የመኪና መለዋወጫ ፣ ለሆቴል እና ቱሪዝም ስልጠና መስጫ እቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢ ንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር መከፈላቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታከስ ከፋይነት ማረጋገጫ (TIN) መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600/ስድስት መቶ ብር ብቻ/ በኢትየጵያ ንግድ ባንክ እ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000133257498 ወይም በአካል ኮሌጁ ድረስ በመቅረብ ገቢ በማድረግ ይህን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግ/ን/አስ/ደጋፊ ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊ ባንከ የተረጋገጠ ብር 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ CPO/ በአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮለጅ ስም አሰርቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. አሸናፊ ተጫራቶች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና የውሉ ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆኑባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ በሚገዙት የጨረታ ዶከመንት ላይበመሙላት ዋናው ኦርጅናል/ እና ኮፒው ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስምና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስምና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡ 00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ወይም ተወዳዳሪ ለውድድር ዋጋ ሞልተው የሚያቀርበው ኮሌጁ በአዘጋጀው የጨረታ ዶከሜንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክሜንት ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ መደረግ አለበት ፡፡
8. ተጫራቾች ከጨረታ ዶከመንት ጋር ተያይዞ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ጨምሮ ማንኛውም መረጃ ለውድድር ከሚቀርቡ ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንቶች ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት ፡፡
9. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀን በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝቲም ከፍል ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል
10. እሸናፊው ውል ተፈራርሞ ከአጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ12 ቀናት ውስጥ የአሸነፈባቸው እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጅ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
12. ተጫራቶች የሚያቀርቡት የዋጋ ሁኔታ VAT የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርበታል ፡፡ በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ነው ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0113110554/0113110424
የአረቅጥ ፖ/ቴ/ኮሌጅ
