በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር APPF/NCB/02/18
1. በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
LOT 1. የተለያዩ የምርት ማሸጊያዎች
LOT 2. PIT (Information Technology) ዕቃዎች
LOT 3. የተለያዩ የሰራተኞች የሥራ አልባሳት
LOT 4. የፅህፈት መሳሪያ (Stationary) እቃዎች
LOT 5. የተለያዩ የፅዳት እቃዎች
LOT 6. የተለያዩ የሥራ ቦታ አደጋ መከላከያ እቃዎች
LOT 7. የተለያዩ ለላቦራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ የላቦራቶሪ እቃዎች
LOT 8. የተለያዩ ተሸከርካሪ ጎማዎች (TYRE FOR DIFFERENT VEHICLES)
LOT 9. የተለያዩ የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች
LOT 10. የተለያዩ ማሸነሪዎች መለዋወጫ እቃዎች
2.ተጫራቾች የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ለሚከፈልባቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይሰርተፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ፖርታል ላይ በአቅራቢነት መመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኢምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመከፈል ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4.ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትከከል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
5.ከLOT 1 - 3 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከLOT 4-10 ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6.ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7.ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው የቴከኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8.ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መከፈቻው እለት ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል፡፡
9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- ኢአ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 አ/አ፣ አዳሚ ቱሉ 0464419164(ማዞሪያ) 0468410447 (ንግድ መምሪያ) ፓ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ): 247 (አ/ቱሉ)
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ
