የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ የማሸግ አገልግሎት እና የእሸጋ ጥራት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- NEBE/NCB/02/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ የማሸግ አገልግሎት እና የእሸጋ ጥራት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል።
ሎት አንድ፡- የአይሲቲ ቁሳቁስ 20 ሺህ የታብሌቶች 5 በ የማሽግ አገልግሎት እና የ55 ሺህ የሰነድ እና ቁሳቁስ ሳጥኖች የማሸግ አገልግሎት ግዥ
ሎት ሁለት፡- 20 ሺህ ታብሌቶች 5 በ1 መታሸጋቸው እና የ55 ሺህ የሰነድና ቁሳቁስ ሳጥኖች የእሸጋ ጥራት ሂደት የማረጋገጥ አገልግሎት ግዥ
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ) በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ድረ-ገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል ፈርማ መኖር ይገባዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት ለሎት አንድ ብር 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ) ለሎት ሁለት ብር 30,000.00 ብር (ሰላሳ ሺህ) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ታጎሳስ 06 ቀን 2018 ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መከፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
- ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻችን፡ ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 251 115153468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
