Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ /አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ /አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህም፡-

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ጃኬት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ 2017/2018 . ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
  7. ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚስረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 430 ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና የናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ግምገማ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 553 0767 / 011 515 7337

 

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender