ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.
National Insurance Company of Ethiopia S.C.
የተጎዱ ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪዎች ቅሪት አካላት
እና ሌሎች ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ጨረታ
የጨረታ ቁጥር 04/25
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ከዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆኑ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. 4:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ንብረቶቹን ከህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. 4:00 ሰዓት ድረስ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
- የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ተ.እ.ታ ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተ.እ.ታ ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.) ወይም በእንግሊዝኛ NATIONAL INSURANCE CO. OF ETHIOPIA (S.C.) ስም በማንኛውም ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ ከህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. 4:00 ሰዓት ላንቻ ባቡር ጣቢያ ፊት ለፊት ዘፍኮ ሕንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 በሚገኘው የሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ሥራ አመራር መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት በ4፡30 ሰዓት ላይ ከሃና ማርያም ወደ ቃሊቲ አደባባይ በሚወስደው ቀለበት መንገድ ከቻይና ጠጠር መፍጫ ፊት ለፊት በስተግራ በኩል የአጠና መሸጫ አጠገብ ከሚገኘው የኩባንያው የንብረት ማከማቻ ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ
ስልክ 011-466-11-29/0114-65-56-05
