የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከጥር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ሀሞት መሸጥ እና በድርጅቱ ዙሪያ የተሰሩ ሁለት የኮንቴነር ሱቆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት አመት ማከራየት ይፈልጋል።
የዳልጋ ከብት ሀሞት ሽያጭ እና የሱቅ ኪራይ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከጥር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ሀሞት መሸጥ እና በድርጅቱ ዙሪያ የተሰሩ ሁለት የኮንቴነር ሱቆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት አመት ማከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ለዳልጋ ከብት ሃሞት በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብርከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ ያለበት ሲሆን ለኮንቴነር ሱቆች ከውል በኋላ ንግድ ፍቃድ ማውጣት የሚፈልግ ግለሰብ/ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
- የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት ሃሞት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ለኮንቴነር ሱቆች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረስኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል::
- ምርቱን ለመግዛት እና የኮንቴነር ሱቆቹን ለመከራየት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ሀሞት ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እና ለኮንቴነር ሱቅ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!
