በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች በሎት ተከፋፍሎ የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች በሎት ተከፋፍሎ የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በብር |
|
ሎት አንድ |
||
|
1 |
Wheel Loader Engine Rated Power 162 Kw Bucket Capacity 25-3 m³ |
100,000 |
|
2 |
Shower Truck 250Hp Loading Capacity mim 10 m3 |
100,000 |
|
3 |
Garbage Tra/po/com/Dump Truck 330 hp |
100,000 |
|
4 |
EV Automobile Model EV5,2024 |
100,000 |
|
5 |
EV Automobile E2 405 Luxury 2025 |
100,000 |
|
6 |
EV Automobile Model 2024 (ID.6) |
100,000 |
|
7 |
EV Automobile 4X 2025 |
100,000 |
|
8 |
EV Automobile Plus Ev 2025 |
100,000 |
|
9 |
3.5 Tons carry truck |
100,000 |
|
ሎት ሁለት |
||
|
1 |
የተለያዩ የመኪናና የማሽነሪ ጎማዎች |
200,000 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት /Tin Number/ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት
- ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሀዋሳ በሚገኘው የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 307 ለሎት አንድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ለሎት ሁለት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በአካዉንት ቁጥር 1000337749678 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ለ20 ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 21ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 307 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት አንድ ለእያንዳንዱ ዕቃ 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት 200,000 ብር /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር - 046-212-11-20 መደወል ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ
