የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥልጠና ግብቶች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ከሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥልጠና ግብቶች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ከሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የአውቶሞቲቭ ዕቃዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 (አስር ሺህ)
በዚህ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ መሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑ ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ቲን ነምበር ያላቸው።
- የጨረታ ዋጋ የሚሞላው ከልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በገዙት ሰነድ ላይ ሲሆን የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ሁሉንም መረጃዎች በሚገባ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም አስቸጋሪ ሁኔታ ካገጠመ የቀድሞው ቁጥር ሊነበብ በሚችልበት ሁኔታ በአንድ መስመር ብቻ ይሰርዙ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአቅርቦት ዘርፍ ነጠላ ዋጋ እንዲሁም የግርጌ ድምር በመደመር የጠቅላላውን ዋጋ ማሳየት አለባቸው፡፡ የሚሞሉት የነጠላና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን /VAT/ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ለቋሚ እቃ ለሚሰጠው አገልግሎት ቢያንስ የአንድ አመት ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን አርጅናሉንና ሌሎች ማስረጃዎችን ለብቻው በአንድ ፖስታ፣ ሲፒአ ደረሰኝ በአንድ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በማድረግ በሚገባ በማሸግ በጀርባቸው ላይ ኦርጅናል ኮፒ እንዲሁም ሲፒኦ በሚል መግለጽ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋ በሞሉበት የጨረታ ሰነድ በእያንዳነዱ ገጽ ላይ እና በየደረጀው በታሸጉት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን የበላይ ኃላፊ ፊርማ፣ ሥም እንዲሁም ሕጋዊ ክብ ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘረው መሰረት የሞሉትንና ያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር የሥራ ቀናት) በመንግስት የሥራ ሰዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀውና በኮሌጁ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ በተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ ቢገኙ ወይም ለመፈጸም ቢሞክሩ በኢትዮጽያ ሕጎች የተደነገገው ተፈጸሚ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሂደት ለማዛባት ቢሞክሩ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ በቀጣይም በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ የሚመለስ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ለኮሌጁ ግዢ ባዘጋጀው ክፍል በአደራ ማስረከብ አለባቸው፡፡
- ናሙና ሲያመጡ (ሲያቀርቡ) የድርጅቱ ማህተም መደረግ የለበትም ነገር ግን ምልክት ያቀረበ አቅራቢ ያመጠው ናሙና ተቀባይነት የለውም ፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ተጫራች ውል እስኪገባ ድረስ ተመላሽ አይሆንም ።
- የጨረታ ሳጥኑን በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰው ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግዢ ክፍሉ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በመጀመሪያ በእቃ ጥራት ሲሆን በሁለተኛው ደረጃ የሚያቀርቡት ዝቅተኛ የዋጋ መጠን ሆኖ ሁለት ተጫራቾች እኩል ነጥብ ቢያመጡ የግዢ መመሪያና ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10/100 (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ውል ሲፈጸምም ሆነ ከተፈጸመ በኋላ በጨረታው ሰነዱ ላይ ከሞሉት ዋጋ ውጪ ምንም አይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጸምላቸው እንዲያቀርቡ የተዘዙትን እቃ በታዘዙበት ጊዜ በራሳቸው ወጪ ኮሌጁ ግቢ ውስጥ ንብረት ክፍል በማቅረብ ሙሉ በሙሉ ሲያስረክቡና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሲያቀርቡ ነው።
- በግዢ አፈጻጸሙ ላይ በደል ደርሶብኛል የሚል ተጫራች ለአቤቱታው መሰረት የሆነውን የመጨረሻ ውሳኔ ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 /አምስት /የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታ ላወጠው የመንግሥት መ/ቤት የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የበላይ ኃላፊ መልስ ካልሰጠ ወይም በሚሰጠው መልስ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ውሳኔው መሰጠት ከነበረበት ጊዜ ገደብ ማብቂያ ጀምሮ በሚቆጠር 5/ አምስት / የሥራ ቀን ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ለአጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ለአጣሪ ኮሚቴ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ ከተጫራቹ ጋር ከገባው የግዢ ውል አቅርቦት መጠን ላይ በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀር እስከ 20/100 (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 0911357170 ወይም ቢሮ ቁጥር 07 በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ወይም አቅራቢው ድርጅት የአሸነፈበትን እቃ ገቢ ለማድረግ ደረሰኝ ሲያቀርብ የካሽ ሪጅስተር ከአታችመንት ጋር (የእጅ በእጅ ደረሰኝ) ከሆነ ከገቢዎች ደረሰኝ እንዲጠቀሙ የተፈቀደበት ደብዳቤ ማጻፍ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ግን እቃዎን ገቢ ማድረግ የማይቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ከጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈው መምጣት ያለባቸው ከአደራጃቸው የጽ/ቤት የበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገርግን በቡድን መሪ ተፈርሞ የሚመጣ የድጋፍ ደበዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ፤
በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ አቅራቢዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት (እቃ) ብቻ መሆኑን አውቀው የአምራች (አቅራቢ) የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ነገር ግን በማያመርቱት ምርት (እቃ) መወዳደር የሚችሉት እንደማንኛውም ተጫራቾች (ሲ.ፒ.ኦ) ማቅረብ (ማስያዝ) አለባቸው።
የጨረታ ሰነዱን የመይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቀይበት ጊዜ 10 (አሰር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የሥራ ሰዓት በኮሌጁ ግቢ ግዢ ክፍል በቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ለምሳሌ ቢድ ቦንድ፣ የባንክ ጋራንቲ፣ ቢቀርብ በምንም ተቀባይነት እንደማይኖረው እናሳውቃለን፡፡
አድራሻ፡- ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማኅበር ኮካ ኮላ ፋብሪካ
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
