Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ለቢሮ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ለቢሮ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ሎት 1 ኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች ግዥ
  2. ሎት-2 ፈርኒቼር ዕቃዎች ግዥ
  3. ሎት-3 የፅሕፈት መሣሪያዎች ግዥ
  4. ሎት-4 የፅዳት ዕቃዎች ግዥ

በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው

የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸዉ

የተጨማሪ እሴት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸዉን ተክኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ በማዘጋጀት እያንዳንዱን በተናጠል በፖስታ በማሸግ በፖስታዉ ዉጭ ላይ ኦርጅናል / ኮፒ - ብሎ በመፃፍ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) CPO ከተክንካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ | Specification / ሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 005 በመቅረብ 100 (መቶ ብር ብቻ) በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በድርጅቱ በዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ በሌም በታሸገ ኤንቨሎፕ 16ኛዉ ቀን እስከ 600 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 005 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እንድያስገቡ እያሳሰብን ጨረታዉ 600 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀነ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ።

ለበለጠ መረጃ፡ በስልኪቁጥር 0462121127/0462121126

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ

Save Tender