የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የከተማ አስተዳደሩ በ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የከተማ አስተዳደሩ በ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ አሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ
