የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 009/2018ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- ሎት 1 የሙዚቃ መሣሪያዎች እቃ ግዥ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 2 ዩፒኤስ ግዥ
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
- ሎት 4 የካሜራ ማስቀመጫ ሼልፍ ግዥ
- ሎት 5 የአልባሳት ኪራይ አገልግሎት ግዥ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 6 የስፖርት ትጥቅ በድጋሚ የወጣ
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.በ.ግ.ጨ. 009/2018ዓ.ም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ -
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና በፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ሎት1 =50,000 ብር፣ ለሎት2 =200,000 ብር፣ ለሎት3 = 50,000 ብር፣ ለሎት4 =50,000 ብር፣ ለሎት5 = 20,000 ብር፣ ለሎት6 =60,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 6 ለሰነዱ 300 (ሦስት መቶ ብር) ክፍያ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 28 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ለመከፈት አያግደውም፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን/ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሽግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማኅበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ሕንፃ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111116382 መደወል ይችላሉ፡፡
የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ
