የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከጥር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስክ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ሀሞት እና ክጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚያመርተው የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የተረፈ ምርት ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከጥር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስክ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ሀሞት እና ክጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚያመርተው የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት ሃሞት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር)፤ ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል::
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት ሦስት ቀን (ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
- ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ሀሞት ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ለስጋና አጥንት መኖ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ለዳልጋ ከብት ቀንድ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እና ለተነጠረ ሞራ ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!
