የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለዘር ማበጠሪያ ማሽን (Seed Cleaning Machine) የተለያዩ የመለዋወጫ ዕቃዎች (Spare Parts) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE/
NCB/013/2018(በድጋሚ)
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለዘር ማበጠሪያ ማሽን (Seed Cleaning Machine) የተለያዩ የመለዋወጫ ዕቃዎች (Spare Parts) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን
ተጫራቾች፡-
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
- የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡-
ስ.ቁ 011-416 0309/ 011-466-2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት
ከሰኞ-አርብ ጥዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
