የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎት1 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እቃዎች፣ ሎት 5. የስፖርት ማሠልጠኛ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎት1 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እቃዎች፣ ሎት 5. የስፖርት ማሠልጠኛ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሚመለከተው የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የግዥው የብር መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ለዚህም ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከ1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 ብር በመክፈል ከ18/04/2018ዓ.ም እስከ 03/05/2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ04/05/2018 ዓ.ም 3፡35 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠ/ዋጋ 15% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማርኛ የተተረጎመ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለበት። በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ በውስጥ ገቢ ደረሰኝ መቁረጥ አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አሸናፊ የሚለየው በድምር ዋጋ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጎ/መ/ት/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር GI በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎንደር/መም/ትምህርት ኮሌጅ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
