በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ዕቃዎችን መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚሰጡ፡-
- የጽህፈት መሣሪያ እና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን
- ህንፃ መሣሪያዎችን
- የቢሮ ወንበርና ጠረጴዛዎችን
- የመኪና ጎማዎችን
መስፈርቶችን ከሚያሟሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN-NO/ ያላቸው
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በመረጡት ዘዴ ማለትም በባንክ በተመሰከረ CPO በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንከ ዋሰትና ማቅረብ ይችላሉ
- የጨረታ ሰነዱን ጊዶሌ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የገዝዙትንም ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመጻፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተቋሙ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውሰጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ በ16 ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ካሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋለ አሸናፊው የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባትና በገባው ውል መሠረት ዕቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ከፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
- ተቋሙ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467740595/360/021/359 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጊዶሌ ማረሚያ ተቋም
