የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የተለያዩ የተሸከርካሪ ጎማዎችን
- ሎት 2 የማዋለጃ አልጋ /Delivery Coach/
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት/TIN Number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል መሆን ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዥያ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመክፈል ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ከፍያ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ / የባንክ ዋስትና/ ለእያንዳንዱ ሎት
- ለሎት 1 የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎችን 100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ
- ለሎት 2 የማዋለጃ አልጋ /Delivery Coach/ 100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / ብቻ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም /በመጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1/አንድ/ ኦሪጂናል እና 2/ሁለት/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸዉን፣ አድራሻ፣ ማህተምና ፊርማቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መ/ቤቱ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት ሂደቱን አያስተጓግልም።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 47 345 0879 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ታርጫ
