Tender Detail

Tender Details


የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በ2018 ዓ.ም በጀት አመት 2ኛ ዙር ግዥ ለማካሄድ የወጣ ግልፅ ጨረታ


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በ2018 ዓ.ም በጀት አመት 2ኛ ዙር ግዥ ለማካሄድ የወጣ

ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

ሎት 1 የጥገና ዕቃ፣ሎት 2. ደንብ ልብስ ሎት 3 የፅህፈት መሣሪያ ሎት 4 የፎቶ ኮፒእና የፕርንተር ቀለም

ሎት 5. የህትመት ስራዎች፣ ሎት.6 ሞንታርቦ የሙዚቃ ዕቃ፣ሎት 7. የመኪና ጌጣጌጥ ሎት8, የመኪና ማሸፈኛ መረብና ድንኳን፣ ሎት9. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት1ዐ. የዲኬርዕቃዎች ሎት 11 የአይት ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው:-

1. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ፤የንግድ ምዝገባ ምስከርወረቀት፣የአቅራቢነት ሰርተፈኬት በዘርፍ ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2.የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢነትና የግብር መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚወዳደረበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስላጣን ከሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

5. ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በያንዳንዱሎት 200 ብር በመከፈል የመንግስት ግዥ ቢሮ ቁጥር 6ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችልሉ።

6. ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ቀን 10 የስራ ቀናት - ጀምሮ የመንግስት ግዥ ቢሮ ቁጥር 6ኛፎቅ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7 ጨረታው በወጣው በዘኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በከኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡ oo ሰዓት ላይ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስተኛ /6ኛ/ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ።

9.በራሱ ሰነድ ሞልቶ የሚያመጣ ከሆነ ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናል።

10, ዕቃዎቹ በቀረበው ናሙና መሠረት የጨረታ አሸናፊ የሆነ ማቅረብ የሚችል ።

11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በእያንዳንዱ ሎት መሠረት ማስያዝ ይኖርበታል።

12. ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በግልፅ ተፅፎ ሁለቱንም ማቅረብ አለባቸው።

13. ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ በእራሱ ትራንስፓርት ማቅረብ የሚችል ።

14. የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት የሚኖረው ራሱ በመረተው ምርት ብቻ በሆኑ ።

15. እያንዳንዱ ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በባንክ የተረጋገጠ 5000.00 (አምስት ሺብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

16. በሚያስገቡ ፓስታ ላይ እያንደዳንዱ ሎቱን ጠቅሶ ማስገባት አለበት፡፡

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ፡ አራት ኪሎ በሚገኘው አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ

የአራዳ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

Save Tender