በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ/2018ዓ.ም ሶስተኛ ዙርጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ/2018ዓ.ም ሶስተኛ ዙርጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት አይነቶች |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ህትመት ስራዎች |
1 |
5,000.00 |
|
2 |
ቋሚ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች |
2 |
50,000.00 |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች |
3 |
5,000.00 |
|
4 |
የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች (የጽህፈት መሣሪያዎች) |
4 |
5,000.00 |
|
5 |
ደንብ ልብስ |
5 |
15,000.00 |
|
6 |
ቋሚ ፈርኒቸር ዕቃዎች |
6 |
15,000.00 |
|
7 |
የጥገና እቃዎች |
7 |
15,000.00 |
|
8 |
የመኪና ጥገና ወይም የጋራዥ አገልግሎት |
8 |
5,000.00 |
|
9 |
የዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ |
9 |
5,000.00 |
|
10 |
የህከምና እቃዎች |
10 |
50,000.00 |
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስከ ምዝገባ ያላቸው ፤የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፤ ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ቲን ነበር ያላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ወይም በሚያመርቱት እቃ ብቻ ካደራጃቸው አካል በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ መወዳደርይችላሉ። ተቋማቱ አምራች ባልሆነበት ዘርፍ በዋስትና ደብዳቤ አናስተናግድም።
3. የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር /ብቻ በመከፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁ.7 መውሰድ ይቻላል።
4. ከላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ስም በታወቀ ባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የወሰዱትን ሰነድ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በየሎቱ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሁሉም ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ማንዋል/ፎቶግራፍ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
8. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በጠኛ ቀን በ3፡30 ሠዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 04 አለም ባንክ ጤና ጣቢያ በግልፅ ይከፈታል።
9. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለጨረታ የቀረበ ሳንፕል ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለ በሁለት ወር ውስጥ ሳንፐሉን ካልወሰዱ ለተቋሙ ገቢ ይደረጋል።
1. በሎት 2 እና 6 ሳንፕል በካታሎግ ወይም በፎቶ ግራፍ አጉልቶ በሚያሳይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካላቀረቡ መወዳደር አይችሉም።
12. ማንኛውም ተጫራች ናሙና ሲያመጡ በካርቶን ወይም በማዳበሪያ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው። በፌስታል የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም።
13. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ መመሪያ ሰነድ በየገፁ ፈርመው ከብ ማህተም በማድረግ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡-በኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታ ትሮፒካል የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118-32-59-69
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ
