Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት በ 2018 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኝ ባለ በጀት መ/ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ/ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር /////4//የጨ/ 002/18

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር የፋይናንስ /ቤት የግዥ የስራ ሂደት 2018 በጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኝ ባለ በጀት /ቤቶች በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውነው የእቃና አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በሎት /ምድብ/ የግዥ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1. አላቂ የቢሮ እቃዎች (ስቴሽነሪ) ግዥ
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት 3. የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት 4. የመድረክ ዲኮር
  • ሎት 5. ቋሚ ዕቃ

በመሆኑም /ቤታችን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 በተዘረዘሩት የግዥ ምድቦች መወዳደርና መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች /አቅራቢ/ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

  1. የዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና ተጫራቾች የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው::
  5. የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  6. ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1:- 9,505 ሎት2:- 7,703.14፣ ሎት3:- 3,413 ሎት4- 2,000 ሎት5- 9,777 ለእያንዳንዱ ሎት በአድራሻችን CPO መቅረብ አለበት፡፡
  7. በስራ ክህሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ካደራጃቸው /ቤት ኃላፊ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። ከስራ ዘርፍ ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው፡፡:
  9. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በየሎቱ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ከሎት 1-5 ለተገለጹት ዕቃዎች ሰነዱን በሚያስገቡበት ቀን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  11. ገዢው አካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒዮ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው::
  13. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል /ተመላሽ አይደረግም/፡፡
  14. የእቃ ማስረከቢ በኮ///ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ /ቤት የግዥ/ንብረት/ አስተዳደር ይሆናል፡፡
  15. በሚቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ከውክልናው ደብዳቤ አያይዞ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
  16. /ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና 11ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮ///ከተማ ወረዳ 04 የፋይናንስ /ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  18. የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል፡፡
  19. ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የእረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በተከታታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  20. ተጫራቾች ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ ከመስሪያ ቤቱ የተሸጠላቸውን ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር መመለስ አለበት፡፡
  21. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  22. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

 

አድራሻ፡- ከአየር ጤና ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከትሮፒካል ከፍ ብሎ ወረዳ 4 ህንጻ 1 ፎቅ ፋይናንስ /ቤት

 

ለበለጠ መረጃ፡- 011-8-33 84 81/ 011-3-69-37-20

 

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር የፋይናንስ /ቤት

 

Save Tender