አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ የግል ማህበር ወሎ ሰፈር ለሚገኘው ባለ B+G+8 ሕንፃ በጽዳት ሥራ አገልግሎት የንግድ ፈቃድና የስራ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
የፅዳት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ የግል ማህበር ወሎ ሰፈር ለሚገኘው ባለ B+G+8 ሕንፃ በጽዳት ሥራ አገልግሎት የንግድ ፈቃድና የስራ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለዚህ፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያመላክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ የታደስ ንግድ ፈቃድ ያለው እና በንግድ ዘርፉ የተሰማራ ሰው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ የሚያቀርብ!
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- TIN (የንግድ መለያ ቁጥር) ያለው እና ማቅረብ የሚችል፣
- ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ያቀረበውን የመጫረቻ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፣
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ይህንን ማድረጉ የተደረሰበት ማንኛውም ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ መሙያ ሰነዱን ብር 300.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሻጭ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ቅርንጫፍ ወሎ ሰፈር ቂርቆስ ክ/ከተማ ኢትዮ ቻይና ወዳጅነት መንገድ አምባሰል ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 በመሄድ መግዛት ይችላሉ
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ከ26/04/2018ዓ.ም ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ (ለስራ ቀን አቆጣጠር ሲባል ቅዳሜ ከጧዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ያለው ጊዜ የአገልግሎቱ ገዥ የስራ ቀን ስለሆነ እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል) ሲሆን ጨረታው በ7ኛው ቀን ማለትም በ04/05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 9፡00 ሰዓት በአገልግሎት ገዥ ዋና መ/ቤት ማለትም አምባሰል ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በጨረታ መክፍት ስነ ስርዓቱ የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት ዋጋ አያሳጣውም።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
አድራሻ- ወሱ ሰፈር አምባሰል ሕንፃ ስልክ ቁጥር 0114-70-03-49 ደውሎ የሚፈልገውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላል።
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
