የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህትመት ውጤቶች ማሰራት ይፈልጋል።
ጨረታ ቁጥር 14/2018
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህትመት ውጤቶች ማሰራት ይፈልጋል።
- አጀንዳ የ2019 (2026/2027)
- ካሌንደር የ2019 (2026/2027)
- የመልካም ምኞት መግለጫ ካርድ (Greeting Card) የ2019 (2026/2027)
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN NO) ያላቸው፡፡
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 26/5/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ ቀን 26/5/2018 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር - 011-551-32-88
ፖ.ሣ.ቁጥር 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
