የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮዎች መስኮት አገልግሎት የሚውል የመጋረጃ ጨርቅ ከነሙሉ አክሰሰሪዎች እና ከነገጠማው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) እና ብዛት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የመጋረጃ ጨርቅ ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/6/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮዎች መስኮት አገልግሎት የሚውል የመጋረጃ ጨርቅ ከነሙሉ አክሰሰሪዎች እና ከነገጠማው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) እና ብዛት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፡ የቫት ተመዝጋቢ ቲን፤ EGP/PPA በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አ.ማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (uncon ditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሣ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል።
ጨረታው ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ፡- +251911984467 ወይም +25149632090
ፋክስ 0114-421312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን