በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መልሶ ማቋቋሚያ የተለያዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የምግብ ነክ-ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዥ 179/18
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መልሶ ማቋቋሚያ የተለያዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ/ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
በሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ሰዓት |
|
1 |
የቤት ቆርቆሮ |
በቁጥር |
80,000 |
ሎት- 1
|
500,000 |
በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ይከፈታል። |
|
2 |
የተለያዩ ቁጥር ሚስማርና የቆርቆሮ ሚስማር |
በፖኬት |
25,000 |
|||
|
3 |
ኘላስቲክ ሸራና ጂባ |
በቁጥር |
22,000 |
ሎት- 2 |
50,000 |
በ16ኛው ቀን በ5፡00 ታሽጎ በዕለቱ 5፡10 ይከፈታል። |
|
4 |
ብርድ ልብስ |
በቁጥር |
10,000 |
ሎት- 3 |
50,000 |
በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዕለቱ 8፡10 ይከፈታል። |
|
5 |
የተለያዩ የቤት ቁሳቁስ |
በቁጥር |
35,000 |
ሎት- 4 |
500,000 |
በ16ኛው ቀን በ9፡00 ታሽጎ በዕለቱ 8፡10 ይከፈታል። |
በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
· ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
· በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒ-ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።
· ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 15ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
· ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የማጫረቻ ሰነዶች በአንድነት ፖስታ በማዘጋጀት በ 16ኛው ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡
· ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
· የጨረታው ሳጥን መክፈቻ በ16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
· ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
· ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
· ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ 046-131-0134 ይጠቀሙ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
