Tender Detail

Tender Details

  • Company በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 15 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Spare Parts , Labour Outsourcing Services , Cloth And Shoes

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሰራት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ሎት 1 የደንብ ልብስ

ሎት2.ሌሎች አላቂ ዕቃዎች

ሎት3.የፅዳት ዕቃዎች

ሎት4 የፕላንተ ለማሽነሪና ለመሣሪያ መግዥ እቃዎች

ሎት5.የልብስ ስፌት

ሎት6 የጉልበት ስራዎች

በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስከር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት፡ የደንብ ልብስ 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት2 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 10,000/አስር ሺህ ብር/ ሎት3 የፅዳት ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሎት

4. የፕላንተ ለማሽነሪና ለመሣሪያ መግዥ/ እቃዎች 10,000/አስር ሺህ ብር/ ሎትs የልብስ ስፌት 2,000 ሁለት ሺህ ብር ሎት6 የጉልበት ሥራ ካደራጀቸው ወረዳ ደብዳቤ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት ከሎት እስከ ሎት 5 ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እና በተባለው መሰረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ/ የተከፈለበት በአንዱ ከዋናው ዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4 ጨረታው ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስራ አንድ/11፡0ዐ/ድረስ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታ ሰነድ በኦሪጂናልና ኮፒ በድርጅቱ ከብ ማህተም በማድረግና ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

6. የጨረታው በ1ዐኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው መጠንቀቅ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ዋጋ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦሪጂናልና ሰነዱን ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በጽ/ቤቱ ግዥ ቢሮ ማድረግ አለባቸው ::

8. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፋበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትከክለኛውን እቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡

9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤቱ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በዘኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /CPO/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. በማንኛውም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት፡፡

12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡

13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጀቸው አካል በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል ተፈርሞ የቀረበ ዋስትና መኖን አለበት፡፡

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀከት ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender