Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የላብራቶሪ እቃዎች እና የህክምና እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የህትመት ውጤቶችን፣ ሎት 6 የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ እ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003-2018

 

በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ 2018 በጀት አመት 1 ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የላብራቶሪ እቃዎች እና የህምና እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የህትመት ውጤቶችን ሎት 6 የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 7 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና ጨረታ ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1.     በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin no) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ ለሎት 1 70,000 /ሰባ ብር ብቻ/ ለሎት 2 2,000 /ሁለት ብር ብቻ/ ለሎት 3 2,000 /ሁለት ብር ብቻ/ ለሎት 4 3,000 /ሶስት ብር ብቻ/ ሎት 5 3,000 /ሶስት ብር ብቻ/ ሎት 6 16,000 /አስራ ስድስት ብር ብቻ/ ሎት 7- 16,000 /አስራ ስድስት ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።

5.     ጥቃቅን እና አነስተኛን በተመለከተ በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ከወረዳው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት እንደሚኖረው፣ ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት የተቋቋሙበትን ህጋዊ ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነዉ እሴትን ለሚጨመሩ /አምራች ለሆኑ/ ሥራ ዘርፎች ብቻ መሆኑንን እናሳውቃለን። ይሄንን ማስረጃ ካደራጀው አካል በደብዳቤ ተጽፎ ለማያቀርብ ተጫራች የጨረታ ሰነድ በነፃ እንደማይሰጠው እናሳውቃለን።

6.     የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል።

7.     ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚመረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8.     ማንኛውም ተጫራች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ መሙላት አለበት፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለበት የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት ይህንን መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርጉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

9.     ይህ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው 10ኛው ቀን 1000 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋዉም 10ኛው ቀን 1130 ሰዓት ይሆናል። ጨረታው በግልጽ የሚከፈተው 11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል።

10. የጥገና ስራዎችን በተመለከተ ማለትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች /ቤት ባለሙያዎች የወጣው እስፔስፍኬሽን የጥገና ስራዎች በተመለከተ የሚወዳደሩት በጠቅላላ ድምር በአነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል። ሌሎች የጥገና ስራዎች ወይም እስፔስፍኬሽን በአማርኛ የወጡ ስራዎች ለየብቻ የሚወዳደሩ መሆኑንን እናሳውቃለን፡፡

11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ናሙናውን በመስሪያ ቤቱ 4 ፎቅ በሚገኘው የግዥ ቢሮ 407 ገቢ ማድረግ አለባቸው ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ /ተጫራች/ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል። ቋሚ እቃዎችን በተመለከተ ለማቅረብ ቀላል የሆኑትን በማቅረብ ወይም ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

12. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. /ቤቱ ጨረታውን ከውል በፊት 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ መግዛት ይችላል።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 1 54 73 48 / 011 54 60 29 / 0111 26 80 48 / 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ - ጉለሌ /ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ህንጻ ፊት ለፊት

 

በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ

Save Tender