በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፣ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 2ኛ ዙር
መለያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፣ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት
|
ተ.ቁ |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ |
|
2 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ |
|
3 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ |
|
4 |
የህክምና እቃዎች |
5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ |
|
5 |
የትምህርት እቃ |
5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ |
- እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበት የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡ በቀጣይ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ የተጠቀሰውን ብር ከባንክ በተረጋገጠ /cpo/ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀረብባቸው እቃዎች ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ 10% ከባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ አለበት፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት የአሸናፊውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረገኑ ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ ቁጥር 0118669955
ከጎሮ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ የሚወስድ መንገድ ወደ ቀኝ 2 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል፡፡
ቦሌ ወረገኑ ቅድመ/አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት
