የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ለሰራተኞች ለአንድ አመት የሚያገለግል የላብራቶሪ የዱቤ ሕክምና አገልግሎት ብቻ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር/ኢኢግልድ-002/2018
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ለሰራተኞች ለአንድ አመት የሚያገለግል የላብራቶሪ የዱቤ ሕክምና አገልግሎት ብቻ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማለትም በላብራቶሪ አገልግሎት ብቻ ፍቃድ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር ብቻ) የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ : በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ፒያሳ ከሊፋ ሕንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ) አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2::
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ:- በስልክ ቁጥር 0111-57-24-97 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት /ኢኢግልድ/
