በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎችን፣የህትመት ውጤቶች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች የአዳራሽ እስቴጅ ምንጣፍ የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች፣ የጥገና ዕቃዎች እና የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎችን፣የህትመት ውጤቶች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች የአዳራሽ እስቴጅ ምንጣፍ የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች፣ የጥገና ዕቃዎች እና የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና TIN ሰርተፍኬት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፣
3. ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክርወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ የደንብ ልብስ ብር 8,000፡00 (ስምንት ሽህ ብር)፣ ለሎት ሁለት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና ፅዳት ዕቃዎች 3,000፡00 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት የህትመት ስራዎች ብር 4,000፡00 (አራት ሺህ ብር)፣ ለሎት አራት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የቢሮ መስኮት መጋረጃ የአዳራሽ እስቴጅ ምንጣፍ ብር 15,000፡00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፤ ለሎት አምስት የመረጃ ቴክኖሎጅ ዕቃዎች 20,000፡00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) ሎት ስድስት የጥገና ዕቃዎች 4000፡00 (አራት ሺህ _ ብር]፣ሎት ሰባት የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች 6,000፡00 (ስድስት ሺህ ብር) ሲፒዮ (CPO) ወይም የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቅሎ ቤት (ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት) ዳቢ ቤኛ ታወር ከኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎኘ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በከኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት _ በቅ/ጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
8. የጨረታው መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል።
9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0114-70 52 41 /0114-70-58-17
አድራሻ፡- በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቤ ቤኛ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
