የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እቃዎቹ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ ሲሆን፣
· ሎት 1 - አላቂ የ/ጽቤት እቃዎች
· ሎት 2 - አላቂ የፅዳት እቃዎች
· ሎት 3 - የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች
· ሎት 4 - የእንስሳት መድሀኒትና እቃዎች
· ሎት 5 - የጥገና እና ዕድሳት እቃዎች
· ሎት 6 - የኤሌትሪክ እቃዎች
· ሎት 7- የተለያዩ አላቂ የምርምር እቃዎች
· ሎት 8 - የላብራቶር ኬሚካል
ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ላሉት 20 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ21 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፍት አያስተጓጉልም። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈፀም ማዕከሉ ድረስ በ15 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማዕከሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ተያይዘዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ 011-673-69-18
የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል
